የአብን እጩ ተወዳዳሪ መገደላቸውን ፓርቲው አስታወቀ!

የአብን እጩ ተወዳዳሪ መገደላቸውን ፓርቲው አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) አባል አቶ በሪሁን አስፈራው መተከል ዞን ውስጥ ግድያ እንደተፈፀመባቸው ፓርቲው አስታውቋል።

አብን ዛሬ ባወጣው የሀዘን መግለጫ እንዳለው፣ አቶ በሪሁን ግድያ የተፈፀመባቸው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያሉ ልዩ ቦታው “ካርባር” በሚባል ቦታ ላይ ሲሆን፣
ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ማድረጋቸውን ነገር ግን በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን መቻሉንና የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎች ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቹ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ መከራ መደረጉን ፖርቲው በመግለጫው አመልክቷል።

“የእጩ ተወዳዳሪ አቶ በሪሁን ግድያ ፖለቲካዊ መሰረት ያለው እና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ “ሆነ ተብሎ” የተደረገ እንደሆነ እንደሚያምን” የገለፀው አብን፣ መንግስት በምርጫ እጩ አባሉ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቋል።

LEAVE A REPLY