ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አስመልክተው ዛሬ መግለጫ የሰጡት ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ በትግራይ ክልል በስምንት የተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ የሽፍታ ቡድን በአገር መከለከያ ሰራዊት እርምጃ እንደተወሰደበት ተናግረዋል።
ጄነራሉ በዚሁ በመግለጫቸው በትግራይ ክልል የአገር መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትኖ የሚገኘውን የጁንታውን ታጣቂ ኃይል በማደን በኩል የነበረውን ሁኔታ አብራርተው፣ በዚህም በክልሉ በስምንት የተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ ቡድን ላይ እርምጃ መወሰዱንና በአካባቢው የነበሩ ማሰልጠኛዎችም ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል። የቀሩት የሽፍታው ቡድን አባላት እጃቸውን ለአገር መከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውንም ተናግረዋል።
“ጥቂት የቡድኑ አባላትና አመራሮችም ተስፋ በመቁረጥ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ሙከራ አድርገው ነበር” ያሉት ሌተናል ጄነራል ባጫ፣ “ይሁን እንጂ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል” ሲሉም ገልፀዋል።