በፓስፖርት ጉዳይ በህገወጦች የማጭበርበር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ!

በፓስፖርት ጉዳይ በህገወጦች የማጭበርበር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ!

 

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየኢ.ፌ.ዴ.ሪ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የፓስፖርት አገልግሎትን ተገልጋዬች ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላየን ምዝገባ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውሶ “ተገልግላዮች በማንኛው አካባቢ ባለና ኢንተርኔት አገልግሎት ባለበት የሞባይል ስልክ ወይም ኮምፒዩተር ላይ በመጠቀም www.ethiopianpassportservices.gov.et የሚለውን ሊንክ ተከትለው በእራሳቸው ወይንም በሌላ ቅርብ የቤተሰብ አባል ወይም በጓደኛ እንዲሞሉላቸው ማድረግ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።

ክፍያው የሚፈፀመውም በባንክ አማካኝነት ስለሆነ ቀጠሮ ለመያዝ ወደኤጀንሲው ቢሮ ተገልጋዩ በአካል መምጣት አይጠበቀበትም” በማለት በሰጠው መግለጫ፣

ይሁንና “የኦንላየን አገልግሎት እንሰጣለን በማለት በኤጀንሲው ዙሪያ ያሉና የክፍያ አገልግሎት ያለአግባብ የሚጨምሩ ፣ የተገልጋዩን መረጃ በጥራት የማይሞሉ፣ የተገልጋዩን ሳይሆን የራሳቸውን ስልክ ቁጥር በተገልጋዩ መረጃ ላይ በመፃፍ ለተገልጋዩ ተገቢው የፅሁፍ መልእክት እንዳይደርሰው የሚያደርጉ፣ እንደልደት ምስክር ወረቀትና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ያሉ አስፈላጊ መረጃዎችን በማጓደል ተጨማሪ ክፍያ የሚያስከፍሉ፣ የተጭበረበረ እና በሚመለከተው አካል ያልተረጋገጠ የልደት ሰርተፍኬት ከሚያቀርቡ ህገወጥ ደላሎች ስላሉ ተገልጋዩ እራሱን እንዲጠብቅ” ሲል ኤጀንሲው አሳስቧል።

 

LEAVE A REPLY