የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ሀገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ ነው ተባለ!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ሀገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ ነው ተባለ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአለም ጤና ድርጅት የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል (CDC) እና ከኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመተባበር ነው ጥናት የሚከናወነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኮቪድ -19 ስርጭት በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጥናት በማካሄድ በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ላይ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያስችላል የተባለለትን የዳሰሳ ጥናት ከሚያዚያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር እንደሚያካሂዱ ገልፀዋል፡፡

ጥናቱን በማስመልከት ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡት የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 የምርምር አማካሪ ዶ/ር አበባው ገበየሁ እንደተናገሩት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የኮቪድ-19 ጥናት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሀገር አቀፍ ደረጃ ምን እንደሚመስል በዋናነት እንደሚያተኩር ታወቋል።

በአካባቢ፣ በእድሜ፣ በጾታ ስርጭቱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚተንትን እንዲሁም ምልክት ሳያሳዩ ታመው የነበሩ፣ በበሽታው የተጠቁት የህብረተሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች፣ ተጋላጭ የሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እነማን እንደሆኑ በጥልቀት የሚመረምር ወሳኝ ጥናት መሆኑ ታምኖበታል፡፡

LEAVE A REPLY