የግድቡን ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ ለማድረግ እንቅስቃሴ መኖሩ ተነገረ! ግብጽ የውሃ ሙሌቱ...

የግድቡን ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ ለማድረግ እንቅስቃሴ መኖሩ ተነገረ! ግብጽ የውሃ ሙሌቱ ተፅዕኖ አይፈጥርብኝም አለች!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንትና በሰጡት መግለጫ፤ የህዳሴ ግድብን የውሃ ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት መኖሩን አመልክተው “የዓባይን ወንዝ ጉዳይ አጀንዳው ወደማይመለከተው አካል ይዞ ለመሄድ የሚደረገው ጥረት ፍጹም ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሦስቱ አገራት የሚያካሂዱት ድርድር የሚፈታው በሌሎች አካላት ሳይሆን በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ ውስጥ መሆን አለበት የሚለው የኢትዮጵያ የፀና አቋም አሁንም እንደተጠበቀ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አረግጠዋል።

የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የሌሎችን አገራት መልዕክት ይዞ በመንቀሳቀስ የግድቡን አጀንዳ ወደ ሌሎች አገራት የመውሰድ አዝማሚያ ማሳየቱን የተናገሩት አምባሳደር ዲና፤ ሱዳን የራሷ አጀንዳ ሳይኖራት ስለግድቡ ጉዳይ የተሳሳተ አቋም መያዟ ስህተት መሆኑን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ግዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በግብጽ ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደሌለ ካለም ያንን ለመቋቋመ የሚያስችል በቂ ውሃ እንዳላት የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ በአስዋን ግድብ በቂ ውሃ መያዛቸውንም ለሀገራቸው ፓርላማ አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY