በ2014 ዓ.ም በሁሉም ት/ቤቶች ከ1ኛ-12ኛ ክፍል የቴአትር ትምህርት ሊሰጥ ነው!

በ2014 ዓ.ም በሁሉም ት/ቤቶች ከ1ኛ-12ኛ ክፍል የቴአትር ትምህርት ሊሰጥ ነው!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከአንደኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል የቴአትር ትምህርት በ 2014 ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የቴአትር ትምህርቱን መስጠት ያስፈለገው “ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ የመግባባት ችሎታቸውን እንዲገልፁ፣ ማመዛዘንና ማሰላሰላቸውን እንዲያጎለብቱ፣ በጎ አስተሳሰቦችን እንዲያዳብሩ፣ የተፈጥሮ ችሎታቸውን እንዲገልፁ፣ በሰው ፊት የመናገር ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ ቀና አስተሳሰብ እንዲኖራቸውና አገራቸውን እንዲወዱ” ለማስቻል መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ የማስተማሪያ መፅሐፍት ዝግጅት መጠናቀቁም ተነግሯል።

ትምህርቱን ለማስጀመር 3000 መምህራን እንደሚያስፈልጉ የገለፁት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል መምህር እና የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ የመምህራን ዕጥረቱን ለመቅረፍ በቴአትር ተመርቀው በስራው ያልተሰማሩትንና በየክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን ለማሳተፍ መታሰቡን አመልክተዋል።

LEAVE A REPLY