ሱዳን “61 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዣለሁ” ማለቷን ኢትዮጵያ አስተባበለች!

ሱዳን “61 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዣለሁ” ማለቷን ኢትዮጵያ አስተባበለች!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሱዳን “ከሰሞኑ 61 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር አውያለሁ” በማለት ማስታወቋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “መሠረተ ቢስ ነው” ሲል ምላሽ ሰጥቶበታል።

“ሱዳን ምንም አይነት የኢትዮጵያን ወታደር በቁጥጥር ስር አላዋለችም። የኢትዮጵያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ አሁንም ድረስ አልወጣም። በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረ ምንም አይነት የጦርነት እንቅስቃሴ የለም። ሱዳን ግን የድንበሩን ጉዳይ ቀጠናዊ ለማድረግ እየሰራች ነው” በማለት ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የገለፁት ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “ሱዳን ትንኮሳዋን ብትቀጥልም ኢትዮጵያ ግን አሁንም የድንበር ጉዳዩን በዲፕሎማሲ የመፍታት እምነት አላት” ብለዋል።

ሱዳንና ግብፅ የህዳሴ ግድቡን የድርድር ሂደት እያደናቀፉ እንደሚገኙና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአገራቱ ላይ ጫና እንዲያሳድር የኢትዮጵያ መንግስት በደብዳቤ መጠየቁን ያወሱት አምባሳደር ዲና “ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካዊያን መፈታት ይችላሉ የሚል የፀና አቋም ስላላት የአፍሪካ ህብረት በአደራዳሪነት እንዲቀጥል እየሰራች ትገኛለች። ግብፅና ሱዳን የድርድር ሂደቱን ከአፍሪካ ህብረት ለማስወጣት የሚያደርጉ ጥረትም በኢትዮጵያ ፍፁም ተቀባይነት የለውም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY