ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ኦስማን ዲዮን ዛሬ ባካሄዱት ስምምነት የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሶስት የልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ፣ የ907 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።
የፊርማ ስነ ስርዓቱን የፈፀሙት የሁለቱ ወገን ተጠሪዎች በስነስርዓቱ ላይ እንደገለፁት ከ907 ሚሊዮኑ ውስጥ፣ 200 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙና በአነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ለተሰማሩ፣ 500 ሚሊዮን ዶላር በሀገሪቱ ለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትና ለግሉ ዘርፍ የካፒታል ተሳትፎንና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን ለማምጣት፣ እንዲሁም 207 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ – 19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የበሽታው መከላከያ ክትባቶችን ውጤታማ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲዳረስ ለማድረግ የሚውል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።