በካዛንቺስ ግንባታ ላይ የነበረ ሕንፃ ተደርምሶ የሰዎች ሕይወት አለፈ!

በካዛንቺስ ግንባታ ላይ የነበረ ሕንፃ ተደርምሶ የሰዎች ሕይወት አለፈ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ ካሳንችስ አካባቢ በሚገኘው ሃናን ዳቦ ቤት ፊለፊት ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ሰዓት ገደማ በግንባታ ላይ የነበረ ጅምር ህንፃ በመደርመሱ ምክንያት እስካሁን ድረስ የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።

የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ባይታወቅም በስፍራው በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ 3 ሰራተኞች ህይወታቸው እንዳለለፈ በአንድ ሰው ላይ ከባድ፣ በሶስቱ ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አደጋው በደረሰበት ስፍራ ቁጥራቸው ከ115 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች በግንባታ ስራ ላይ እንደነበሩ በቦታው ተገኝቶ ያረጋገጠው ዘጋቢያችን፣ 35 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በ3 ከባድና 4 ቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም 3 አምቡላንሶች እየታገዙ በናዳ ምክንያት የተቀበሩ ሰዎችን ለማውጣትና የተጎዱትን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ሲያደርጉ መመልከቱን ገልፆልናል።

LEAVE A REPLY