ሱዳን “2ኛው ዙር ውሃ ሙሌት ከተከናወነ በኢትዮጵያና በሳሊኒ ላይ ክስ እመሰርታለሁ” አለች!

ሱዳን “2ኛው ዙር ውሃ ሙሌት ከተከናወነ በኢትዮጵያና በሳሊኒ ላይ ክስ እመሰርታለሁ” አለች!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሱዳን የመስኖ እና የውሃ ሀብት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ያለሕጋዊ ስምምነት የሚከናወን ከሆነ፣ አገራቸው የግድቡን የሲቪል ግንባታ ማከናወን ላይ በሚገኘው የጣሊያን ኩባንያ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ክስ እንደምትመሰርት አስታውቀዋል፡፡

“ክሱ የሚመሰረተው ግድቡ በሚያስከትላቸው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተፅእኖዎች እና አደጋዎች ላይ ጥናት ባለመደረጉ ነው።

እስካሁን ስምምነት ላይ አለመደረሱ፣ የግድቡ ጉዳይ በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ላይ ስጋት የደቀነ በመሆኑ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት አቤቱታ ለማቅረብ መንገድ ይከፍትልናል” ያሉት ሚኒስትር ያሲር አባስ፣ “ሁለተኛው ሙሌት ሕጋዊ ስምምነት ሳይደረስ የሚከናወን ከሆነ፣ ሱዳን በዓለም አቀፍ የሕግ ቢሮዎች የሚደገፉ የሕግ ቡድኖቿን በመጠቀም በጣሊያኑ ኩባንያ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ክስ ትመሰርታለች” ብለዋል።

“ስምምነት ላይ መድረስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ወይም መብት አይቀንስምም፤ ነገር ግን ለሱዳን ሙሉ መብት ይሰጣል ጥቅሟንም ያስጠብቃል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል፡፡

LEAVE A REPLY