በሀሰተኛ ሰነድ ወደ አገር የገባ 186,240 ገጀራ ተያዘ!

በሀሰተኛ ሰነድ ወደ አገር የገባ 186,240 ገጀራ ተያዘ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የኢፌዲሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው፣ 15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ  ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኋላ በቁጥጥር ስር ተመልክቷል።

እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ 7.7ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ከፍሎ እቃው ከተለቀቀ በኃላ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ /ቤት ኢንተለጀንስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና እቃውም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል::

ጉዳዩ 15 ቀን በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፤ አስመጪው ያቀረብኩት ሰነድ ህጋዊ ነው በማለት ቅሬታ ስላቀረበ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጋር በተደረገው ማጣራት ሰነዱ ሐሰተኛ እና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኛ የእጅ ገጀራው ተገቢውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እንዲስተናገድ የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማውጣት የተሞከረ ሲሆን ይህም ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል” ሲል ሚኒሰትር መሰሪያ ቤቱ አስታወቋል። 

ይህን መነሻ በማድረግም በፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ /ቤት መረጃውን በመስጠት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል የእቃው ባለቤት እና ትራንዚተሩ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።

ገጀራ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች አንዱ መሆኑንና ከፌደራል ፖሊስ ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ማስገባት የተከለከለ እንደሆነ የገለፀው የገቢዎች /ር፣ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በጉምሩክ ኮምሽን ባለሙያ እቃው እንዲወጣ የተፈቀደበት ደብዳቤ በማስመሰልና ሐሰተኛ የደብዳቤ ፎቶ በመጠቀም አስመጪው ሕጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑንም አሳውቋል፡፡

LEAVE A REPLY