ኢሰመኮ “በጅማ እና በደቡብ አማሮ” ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አስታወቀ!

ኢሰመኮ “በጅማ እና በደቡብ አማሮ” ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበጅማ ሊሙ ኮሳ ወረዳ፣ ቀጮ ክርክር እና ጋሌ ቀበሌ እንዲሁም በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ፣ ዳን ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት ማድረሳቸውን የገለፀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቦታዎቹ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል።

በጅማ ሊሙ ኮሳ ወረዳ፣ ቀጮ ክርክር እና ጋሌ ቀበሌ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 / በታጠቁ ኃይሎች ጥቃት መድረሱንና ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን፣ እንዲሁም በተመሳሳይ በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ዳን ቀበሌ በሚያዚያ 22 ቀን 2013 / ታጣቂዎች 6 ሰዎች እንደገደሉ የአካባቢው አስተዳደር ማሳወቁን የገለፀው ኢሰመኮ፣ በኮሳ ወረዳ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ በእለቱ የክልል እና የፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢው መሰማራታቸውን መረዳቱንም አሳውቋል።

የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል ፀጥታ አካላት ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ በቅርበት እየተነጋገርኩ ነውያለው ኢሰመኮ፣ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳትና የሰዎች ሞት እንዳይደርስ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።

በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መብዛታቸው የፀጥታ መዋቅሩ የመከላከል እና ዝግጁነት አቅም ከፍተኛ መሻሻል ሊደረግበት እንደሚገባ የሚያመላክት መሆኑንም ኢሰመኮ አመልክቷል።

LEAVE A REPLY