የደቡብ ክልል ለህግ ታራሚዎች ምህረት አደረገ!

የደቡብ ክልል ለህግ ታራሚዎች ምህረት አደረገ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልላዊ መስተዳድር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ970 የህግ ታራሚዎች ይቅርታና የአስር ዓመት የእስር ቅነሳ ማድረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።

ይቅርታና የእስር ቅነሳ ተደርጎላቸው ከእስር ይለቀቃሉ ከተባሉት ከእነዚህ የህግ ታራሚዎች ውስጥ 903 የሚሆኑት ወንዶች፣ 52ቱ ግሞ ሴቶች ሲሆኑ፣ ለ955ቱም ሙሉ ይቅርታ እንደተደረገላቸው  ተገልጿል።

በተመሳሳይ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ለ2ሺህ 705 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ትናንት መዘገባችን ይታወቃል።

LEAVE A REPLY