“ህወሓት እና ሸኔ ሽብርተኛ” መባላቸውን ለመቃወም የሚያስችል ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀረበ!

“ህወሓት እና ሸኔ ሽብርተኛ” መባላቸውን ለመቃወም የሚያስችል ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀረበ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ህወሓት እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ያስተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ የቀረበለት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ ድርጅቶቹ “ሽብርተኛ” መባላቸውን ለመቃወም የሚያስችል ማስረጃ ካላቸው ለምክር ቤቱ እንዲያቀርቡ የጥሪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ታውቋል።

የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 2ዐ ንኡስ አንቀጽ 2 መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን ሃሳብ የተመለከተው ም/ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ነው ጥሪውን በማስታወቂያ የገለፀው።

“በአዋጁ አንቀጽ 21 ንኡስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሠረት ሁለቱ ድርጅቶች የውሳኔ ሀሳቡን ለመቃወም የሚያስችል ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ካላቸው ይህ ማስታወቂያ በመገናኛ ብዙሃን ከተነገረበት ሰዓት ጀምሮ ባሉት 48 ሰዓታት ውስጥ በምክር ቤቱ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ማቅረብ ይችላሉ” ሲል አስታውቋል።

LEAVE A REPLY