ቀነኒሳ በቀለ በቶክዮ አገሩን ወክሎ እንዳይሳተፍ ክልከላ እንደሚደረግበት ተናገረ!

ቀነኒሳ በቀለ በቶክዮ አገሩን ወክሎ እንዳይሳተፍ ክልከላ እንደሚደረግበት ተናገረ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና:- አትሌት ቀነኒሳ በቀለ “አገሬን ወክዬ እንዳልሳተፍ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተደጋጋሚ ክልከላ እየደረሰብኝ ነው ሲል አሰታወቀ

ያለኝ አንድ አገር ነው፤ ሌላ አገር የለኝም። አሁን ግለሰቦች ቢበድሉኝም አገሬ አልበደለችኝም። ማጣሪያው ላይ ያልተወዳደርኩት በሐዘን ላይ ስለነበርኩና ከሳምንታት በፊት ኮቪድ 19 ይዞኝ ስለነበር ነው። ይህንን ፌዴሬሽኑ ያውቃል” ሲል ተናግሯል።

አትሌት ቀነኒሳ በቅርቡ ከቶኪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ምርጫ ጋር በተያያዘ “ላቀረብኩት ቅሬታ በቂ ምላሽ የማይሰጠኝ ከሆነ በግል የዓለም አቀፉን የኦሎምፒክ ባንዲራ ወክዬ ልወዳደር እችላለሁ” ሲል ገልፆ፣ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2020 ሊካሄድ ታቅዶ በነበረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመወዳደር በአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ተመርጦ እንደነበረ አስታውሷል።

ይሁንና፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሰጠው ምላሽ
በአትሌት ቀነኒሳ ዘንድ ቅሬታን የፈጠረው ጉዳይ
“በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ውድድሮች ስላልተካሄዱ ፌዴሬሽኑ የአትሌቶችን ብቃት ለመለየት የአገር ውስጥ ውድድር በማካሄድ ለመምረጥ ማሰቡ ነው” ብሏል።

LEAVE A REPLY