ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኦቢኤን ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ትናንት ከቀኑ 11፡30 ላይ ከሰርግ ቤት ሲመለስ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በአሸባሪው የሸኔ ሁለት ታጣቂዎች መገደሉን፣ የወንጀሉ ፈፃሚዎች ማንነትም እንደተደረሰበት እና ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ በቄለም ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ሰላም አስከባሪ ምክትል ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አህመድ ያሲን ገልፀዋል፡፡
ጋዜጠኛ ሲሳይ ህዝባዊ ወገንተኝነትን እንዲሁም መልካም ስነ-ምግባርን የተላበሰ ጠንካራ ጋዜጠኛ እንደነበር የስራ ባልደረቦቹ ተናግረዋል፡፡