የጆይ ኦውቲዝም ማዕከል መሥራቿ ወ/ሮ ዘሚ የኑስ በሞት ተለዩ!

የጆይ ኦውቲዝም ማዕከል መሥራቿ ወ/ሮ ዘሚ የኑስ በሞት ተለዩ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኒያ ፋውንዴሽን እና የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራች ወይዘሮ ዘሚ የኑስ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በፅኑ ህክምና ማዕከል ውስጥ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።

የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራቿ ወ/ሮ ዘሚ የኑስ በኮቪድ የህክምና ማዕከል ሆነው “ፀልዩልኝ” አሉ!

በኢትዮጵያ ነገ ዜና፣ ከሳምንት በፊት (ሚያዝያ 20/2013) “ወንድ ልጃቸው የአዕምሮ እድገት ዝግመት ያለበት ሆኖ መወለዱ ስለችግሩ በጥልቀት እንዲረዱና ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች መሰሎችም መፍትሔ ለማስገኘት እንዲነሱ አድርጓቸው፣ በኒያ ፋውንዴሽን ስር ጆይ የኦቲዝም ማዕከል የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት አቋቁመው ለበርካታ ወገኖች ደራሽ መሆን የቻሉት የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራችና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ዘሚ የኑስ፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ተይዘው ፅኑ ህሙማን ማዕከል ውስጥ የህክምና ክትትል እያደረጉ ሲሆን፣ ከማዕከሉ ሆነውም ለመላው ኢትዮጵያውያን “በፀሎት አስቡኝ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።” የሚል ዘገባ መቅረቡ ይታወሳል።

ዝግጅት ክፍላችን ለበርካታ ወገኖች ደራሽ መሆን በቻሉት የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራችና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

LEAVE A REPLY