ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የመከላከያ ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው በሰጡት መግለጫ፣ በትግራይ ክልል የሕግ ማሰከበር ዘመቻ በተጀመረበት ወቅት ማይካድራ ላይ ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ አምልጦ የነበረው ኃይል እንደገና ተደራጅቶ ወደ ሀገር ሊገባ ሙከራ ሲያደርግ መደምሰሱ አስታውቀዋል፡፡
“በሶስት ቡድን የተደራጀው ይህ ኃይል ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ መሆኑንና ሌሎች ኃይሎችንም ከሀገር ለማስወጣት ባደረገው ማጥቃት በሱዳን አምዳይት በኩል በተወሰደ ርምጃ 320ዎቹ ተደምስሰዋል” ያሉት
ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ በተወሰደው ርምጃ በርካታ ትጥቅ፣ ሳተላይት ስልክና ሌሎች ቁሳቁስ መያዛቸውን፣ ከሱዳን ጀነራሎች ጋር ለመስራት የያዘው ሚስጥርም መገኘቱንና የተደራጀው ቡድን በሱዳን፣ አሜሪካና ኢትዮጵያ ላይ ሲሰራ የቆየ መሆኑም ገልጸው “ጁንታው አሁን ያለው ምላሱ ብቻ ነው። የተገዙ አክቲቪስቶች የሚያስተላልፉት የተሳሳተ መረጃ መታመን የለበትም” ብለዋል፡፡