አምነስቲ፤ በአክሱም ከተማ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ዐቃቤ ህግ የሰጠውን መግለጫ አጣጣለ!

አምነስቲ፤ በአክሱም ከተማ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ዐቃቤ ህግ የሰጠውን መግለጫ አጣጣለ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናከቀናት በፊት፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአክሱም ከተማ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ የሰጠውን ዝርዝር መግለጫ፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው መግለጫ አጣጥሎታል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በመግለጫው፣ በአክሱም በነበረ ውጊያ 93 ሰዎች መሞታቸውንና ሟቾቹ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም አብዛኞቹ በጦርነቱ የተሳተፉ መሆናቸው፣ በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበራቸው በመንገድ ላይ የነበሩ ንጹሀንም መገደላቸውን፣ የህወሓት ታጣቂዎች የኤርትራ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀማቸው፣ እንዲሁም በእስር ለነበሩ ወንጀለኞች የኤርትራ ወታደራዊ የደምብ ልብስ በመስጠት ከእስር ቤት መልቀቃቸው በአክሱም ለተፈፀመ ድርጊት ምክንያት እንደሆነ በምርመራ መረጋገጡን ገልፆ ነበር።

ይሁንና፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የጠቅላይ ዐቃቤ ህግን መግለጫ በማጣጣል ራሱ “በምርመራ አረጋግጫለሁ” ያለውን እውነት ይፋ አድርጓል።

ጥቃቱ ያነጣጠረው በታጣቂዎች ላይ ሳይሆን ንፁሀን ላይ ነው። ከሞት ለማምለጥ ሲሞክሩ የነበሩ ንፁሀን መጠቃታቸውንም በምርመራ አረጋግጫለሁ” ያለው አምነስቲ “በኤርትራ ሰራዊት ሲደረግ በነበረ ቤት ለቤት አሰሳ ወጣቶችና አዛውንቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሀን ተገድለዋል፤ እስከ አመሻሽ በቆየው የቤት ለቤት አሰሳ በርካቶች ቤተሰቦቻቸው ፊት ተረሽነዋል” በማለትም አስታውቋል።

“ወንጀሉን በመፈጸም ረገድ የኤርትራ ጦር ሚናን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በልኩ አላስቀመጠም” ሲል የሚወቅሰው የአምነስቲ መግለጫ “ከምስክሮች በቃለ መጠይቅ እንዳረጋገጥኩት የቤት ለቤት አሰሳ ሲያካሂዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ከለበሱት የደምብ ልብስ በተጨማሪ በባህል እና የቋንቋ ዘያቸው ይለያሉ። በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ጭፍጨፋ የመመርመር ኃላፊነት አለበት” በማለትም አመልክቷል።

LEAVE A REPLY