አንድ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሃይቅ ውስጥ ሞቶ ተገኘ! በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ንብረት ወደመ!

አንድ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሃይቅ ውስጥ ሞቶ ተገኘ! በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ንብረት ወደመ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበወልድያ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ምህንድስና ትምህርት ክፍል ትምህርቱን በመከታተል ላይ የነበረና ምኒልክ አበበ የተባለ የ4ኛ ዓመት ተማሪ ሀይቅ ውስጥ ሰጥሞ ህይወቱ እንዳለፈ ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

ተማሪው ከግቢ በመውጣት ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ወደ ሃይቅ ከተማ በመጓዝ እየተዝናኑ በነበረበት ወቅት በሃይቁ ውስጥ ለመዋኘት እየሞከሩ እንዳለ የመስመጥ አደጋ አጋጥሞት ግንቦት 6/2013 ዓ.ም ህይወቱ እንዳለፈ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፣ በደረሰው መረጃ መሠረት ወደ አካባቢው በመጓዝ ሬሳውን በሀይቁ ውስጥ በማፈላለግ እንዳገኘው እና ግንቦት 7/2013 ዓ.ም ወደ ቤተሰቦቹ እንዲደርስ ማድረጉን አሳውቋል።

በሌላ በኩል፣ ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢን ጨምሮ በከተማዋና በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ተቋረጡን ተከትሎ
ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ ተሰብስበው ወደ አስተዳደር ቢሮ ማምራታቸውና የተቆጡ ተማሪዎች
ድንጋይ በመወርወርና የንብረት ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።

በአካባቢው ካለው የሙቀት መጠን ጋር ተያይዞ የመብራት መቋረጥ የሚያስከትለው ዘርፈ ብዙ ችግር መኖሩ፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደምም የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ የውሃ አቅርቦት እጥረት ችግሮች ተደማምረው ተማሪዎቹን ለተቃውሞ ማነሳሳቱ የተመለከተ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ የሰመራ ዩኒቨርስቲ እስካሁን በይፋ የገለጸው ነገር የለም።

LEAVE A REPLY