ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር ግብአት መጠየቃቸው ተገለጸ!

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር ግብአት መጠየቃቸው ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ዛሬ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ባሰፈረው አጭር መረጃ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቴሌኮም ፈቃድ አወጣጥ ሂደትን አስመልክቶ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ከተቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት ግብአት ጠይቀዋል” ሲል ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው “የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዛሬ ጠዋት በተደረገ ውይይት አዲሱን የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ሂደት በዝርዝር አቅርቧል። ይህም ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር የተቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

የዛሬው ስብሰባ የጨረታ ሂደቱን ዝርዝር በግልፅ ያሳየ ሲሆን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት #የኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ እና ወደ ከፍታ የመስፈንጠር ፍላጎቷን የሚያስቀድም ውሳኔ እንዲወስን የሚያስችሉ ግብዓቶች ቀርበዋል” በማለት በማህበራዊ ትስስር ይፋዊ ገፃቸው ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY