ምርጫ ቦርድ ለ45 ተቋማት የምርጫ ታዛቢነት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ!

ምርጫ ቦርድ ለ45 ተቋማት የምርጫ ታዛቢነት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ይፋዊ ገፁ እንደገለፀው፣ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011፣ እንዲሁም “የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012” በሚደነግገው መሠረት፣ ምርጫ ለመታዘብ ፍላጎት ያላቸውን የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይፋዊ ማስታወቂያ በማውጣትና በመመልመል በአንደኛ ዙር ለ36 ድርጅቶችን እውቅና መስጠቱን ገለፀ።

6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መታዘብ እንዲችሉ በመጀመሪያ ዙር አመልክተው ካልተመረጡ የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል፣ ለቦርዱ ይግባኝ በማስገባት ይግባኛቸው በቦርዱ ታይቶ ውሣኔ ከተሰጠባቸው እና በሁለተኛ ዙር እንደ አዲስ ምርጫን ለመታዘብ ማመልከቻ ካስገቡ ድርጅቶች መካከል ዘጠኝ የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፍቃድ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚሁ መግለጫው እንዳለው፣
1. ማኅበረ ሕይወት ኢትዮጵያ – ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት

2. አልቢር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን

3. ዲጂታል ሮግ ሶሳይቲ ኤክስፐርመንት ግሩፕ

4. ስፕሪድ የማኅበራዊ ችግሮች መፍቻ እና የልማት ድርጅት

5. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር

6. ሰኔ 16 የሰላምና የለዉጥ ተምሳሌት የሲቪክ ማኅበር

7. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን

8. የአፍሪካ ልማትና ጥበቃ ተቋም

9. ሶሳይቲ ፎር ኢኮ ቱሪዝም ኤንድ ባዮ ዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን ለተባሉት ዘጠኝ ተቋማት 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መታዘብ እንዲችሉ ፈቃድ መስጠቱ፣ እንዲሁም ከዛሬ ጀምሮ የሚቀርቡ የመታዘብ ሥራ ጥያቄዎችን ቦርዱ መቀበል ማቆሙ ይፋ ሆኗል።

LEAVE A REPLY