ኢትዮጵያን ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ ተገለፀ!

ኢትዮጵያን ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ ተገለፀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያን ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ የገለፀ ሲሆን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንም የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሊት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

ከግድቡ ሙሌት እና ግንባታ ጋር ተያይዞ የአሠራር ሂደቱን “ምንም ዓይነት ኃይል እንደማያደናቅፈው” የገለፀው ሚኒስቴሩ፣ የግድቡ ግንባታ ከ80 በመቶ በላይ መድረሱንም አረጋግጧል።

የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 መድረሱን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት፣ የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል ዶ/ር በለጠ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ የግድቡ የሲቪል ግንባታ 91.8፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታው 54.5 በመቶ፣ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱንም አስረድተው፣ ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚቀረው 20 በመቶ ግንባታ ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል።

በተያያዘ፣ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሊት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ የገለፁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ሁለተኛ ዙር ሙሊት በሶስቱ አገራት የሳይንቲስቶች ብሄራዊ ቡድን በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ፣ በጎረቤት አገራትና ታላላቅ ሃይቆች ክልል የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮኖች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት ጋር በመተባበር “የናይል ፍትሃዊ አጠቃቀም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለክልላዊ ትብብር ያለው ሚና” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ የተሳተፉ መሆናቸውን አመልክተው፣ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑንም ገልፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሶስትዮሽ ድርድሩ በአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት የገለፁ ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ በበኩላቸው፣ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ፕሮጀክት መሆኑን አመልክተው የደቡብ ሱዳን ፓርላማ በቅርቡ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን (CFA) በቅርቡ የሚያፀድቅ መሆኑን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY