በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች መቸገራቸውና መንግሥት 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉ ተነገረ!

በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች መቸገራቸውና መንግሥት 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉ ተነገረ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበትግራይ ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ እንቅስቃሴዎች የሚያደርጉት የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች መቸገራቸውንና የሚገጥማቸው መሰናክልም እየተባባሰ እንደሆነ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ገለፀ።

የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ እና የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እስካሁን ድረስ 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ አስታውቀዋል።

“አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1.8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው” ያለው የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ፣ በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልፆ “እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር፣ እስከ ፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል” ብሏል።

በተያያዘ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የክልሉ ተወላጆች በትግራይ ክልል የሚደረገው አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገሪቱን ብሎም የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈንም መንግሥት በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት ማሳሰባቸው፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ስልክ እና መብራትን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች አገልግሎት እንዲጀምሩም መጠየቃቸው ተመልክቷል።

LEAVE A REPLY