“በትግራይ ተገደለ” በተባለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኛ ጉዳይ መከላከያ ምላሽ ሰጠ!

“በትግራይ ተገደለ” በተባለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኛ ጉዳይ መከላከያ ምላሽ ሰጠ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ፣ ለሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ህይወት እና እንቅስቃሴ ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባና ከ3 ሳምንታት በፊት በትግራይ ቆላ ተንቤን የUSAID አጋር ለሆነ ተቋም የሚሰራ አንድ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኛ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወታደሮች መገደሉን አስታወቋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኛው የተገደለው ማንነቱን ከተናገረ እና እንዳይገሉት ከተማፀነ በኋላ እንደሆነ የአይን እማኞችን ጠቅሶ የገለፀ ሲሆን፣ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በሰጠው ምላሽ “ግልፅ ያልሆነ” ሲል የቀረበውን ውንጀላ አጣጥሎታል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት፣ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነም “ተፈፀመ የተባለው ድርጊት የኢትዮጵያን ወታደሮች የሚገልፅ አይደለም። ምንም ብንሳሳት አትግደለኝ እያለ የሚለምንን የእርዳታ ሰራተኛ፣ ያውም በዚህ ወቅት እንደውም በሰበብ አስባቡ ምክንያት እየተፈለገ በምንወለጀልበት ጊዜ ሊደረግ ይችላል ብሎ ማሰብ በጣም ስህተት ነው” ብለዋል።

LEAVE A REPLY