ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩም፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መስጠቱን የፓርቲው የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ገልፀዋል ።
ይህንን ተከትሎም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው እስክንድር ነጋ “በውሳኔው ደስተኞች ነን። እግዚያብሄርን እናመሰግናለን። ምርጫ ቦርድ የፍ/ቤቱን ውሳኔ አክብሮ እንዲመዘግበንና በህዝብ እንድንመዘን እንጠይቃለን። ምርጫ ቦርድ ወደ ይግባኝ በመሄድ ጉዳዩን እንዳያንጓትተውና የህዝብን የመምረጥ መብት እንዲያከብር በጥሞና እንጠይቃለን” ሲል መልዕክት ማስተላለፉን ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል አስታውቃለች።