እነእስክንድር በምርጫው እንዲሳተፉ በፍ/ቤት መወሰኑን አስመልከቶ ምርጫ ቦርድ ምላሽ ሰጠ!

እነእስክንድር በምርጫው እንዲሳተፉ በፍ/ቤት መወሰኑን አስመልከቶ ምርጫ ቦርድ ምላሽ ሰጠ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩም፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መስጠቱን ተከትሎ፣ ፓርቲው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርግ” ሲል ትናንት ላቀረበው ጥያቄ፣ ቦርዱ ዛሬ ምላሽ ሰጥቷል።

ባልደራስ፣ የፓርቲው አባላት በፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ እንዲፈጸም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ላቀረቡት ጥያቄ ቦርዱ በሰጠው ምላሽ “ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በህግ ጥላ ስር ያሉ የፓርቲው እጩዎች የሆኑት አባላት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 207000 ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ መሰረት እንዲመዘገቡለትና ቦርዱ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ተገቢውን ትዕዛዝ ለምርጫ ወረዳዎች አስተላልፎ እንደፍርዱ እንዲፈፀም ጥያቄ ያቀረበ መሆኑ ይታወቃል።

እንደሚታወቀው የእጬዎች ምዝገባ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በመጠናቀቁ፤ እንዲሁም እያንዳንዱ እጩ ተወዳዳሪዎች በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረውን ስፍራ የሚወስን ሎተሪ እጣ በመውጣቱና፤ በዚሁ መሰረት የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመትም ተጠናቆ ወደምርጫ ጣቢያዎች የመላኩ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚጀመር በመሆኑ፤ እንደውሳኔው ለመፈፀም ቦርዱ የሚቸገር መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን” ብሏል።

ምርጫ ቦርድ ለፍርድ ቤትወሰኔ ተገዥ መሆን እንዳለበት የገለፁ አሰተያየት ሰጪዎች። የፍርድ ቤት ውሳኔን ተግባራዊ እና ፍትሀዊ ለማድረግ ቦርዱ በፈረድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸው ተወዳደሪዎች (እነእስክንድር ነጋ) የሚወዳደሩባቸው ወረዳዎችን የምርጫ ሂደት እሰከማዘግየት መሄድ አለበት ብለዋል።

LEAVE A REPLY