ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በኮቪድ 19 ስቃይ ውስጥ መሰንበቱን አስታወቀ!

ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በኮቪድ 19 ስቃይ ውስጥ መሰንበቱን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበአስገምጋሚ ድምፁ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በኮቪድ 19 ቫይረስ ተይዞ በህክምና ማዕከል ውስጥ መሰንበቱን አሰታወቀ። ጤንነቱ እየተሻሻለ በመሆኑ በቀናት ውስጥ ከሆስፒታል እንደሚወጣ ሀኪሞቹ እንደነገሩትም ዛሬ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

ጋዜጠኛው፣ በሆስፒታል የህክምና አልጋ ላይ ሆኖ፣ አሁንም በኦክስጅን የመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዳ መሆኑን ከሚያሳይ ፎቶ ግራፍ ጋር ዛሬ ባሰራጨው መልዕክቱ “እንደምናደራችሁ?እኔ ደህና። ሐኪሞች ከመጣህ በኋላ ለውጥህ አርኪ ነው ሰኞና ማክሰኞ ቤትህ ትገባለህ የሚል የቅዳሜ መልካም ዜና ሰጥተውኛል። ‘ከደኑ ወጥቻለሁ’/out of the woods already” ፈረንጆቹ እንደሚሉት” ሲል አሰታውቋል

ከዚሁ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ካሳወቀበት መልዕክቱ ጋር “በያላችሁበት መልካም ቅዳሜ ይሁንላችሁ። ትንሽ ጥንቃቄ አድርጉ። ማስክ ልበሱ። ቢያንስ ቢያንስ 1ሜትር ያህል ፈንጠርጠር ብላችሁ ተቀመጡ። በተረፈ እግዚአብሔር አብሯችሁ ይራመድ። ሁኔታው ተለውጦ፣ ቀኑ አልፎ በአየር ላገኛችሁ ጉጉቴ ነው…በጣም!! ከእዚህ ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከእስራኤል ቤርሼባና ሐይፋ…ወገኖቼ በሙሉ አታስቡ፣ ደህና ነኝ” በማለትም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ነገ ዝግጅት ክፍል፣ ተወዳጁ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ከገጠመው ችግር በሰላም ወጥቶ በሙያው አገሩንና ህዝቡን ወደማገልገሉ እንዲመለስ ከልብ ይመኛል።

LEAVE A REPLY