የቅዱስ ሲኖዶስ በዋና ዋና ገዳዮች ላይ ወሳኔ አስተላለፈ! ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ተወስኗል

የቅዱስ ሲኖዶስ በዋና ዋና ገዳዮች ላይ ወሳኔ አስተላለፈ! ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ተወስኗል

ባለ 12 ነጥብ ውሳኔዎች አስተላልፏል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናከግንቦት 17/ 2013 ዓ.ም እስከ ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ሲካሄድ የሰነበተው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ 12 ነጥቦችን የያዙ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠናቋል።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ፓትርያርክ ተክለሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን መግለጫ በንባብ ያሰሙ ሲሆን፣ የውጭ ሃገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሃገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ፣ በሃገር ደህንነት፣ ከቀያቸው ስለተፈናቀሉና ለስደት ስለተዳረጉ፣ በተለያዩ ቦታዎች ስለሚታዩ አለመግባባቶች እና ሌሎች ማህበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይም ውሳኔዎችን አሳልፏል።

“በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የጠፋ የሰው ህይወትና ንብረት በየአህጉረ ስብከቱ ተጣርቶ እንዲቀርብ፣ የአምልኮ ስፍራ፣ ስም እና ተጠብቆ የቆየ የቤተክርስቲያኗ ክብር እንዲሁም በካህናትና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለ ሞትና ስደት ከየአህጉረ ስብከቱ እንዲጣራና መንግስትም አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ፣ የአምልኮ ስፍራዎች በተለይም በዩኔስኮ የተመዘገቡ ስፍራዎችን ልዩ ጥበቃና ትኩረት በመስጠት ከእነማንነታቸው ተጠብቀው እንዲቆዩ መንግስት የበኩሉን እንዲወጣ” ሲልም ሲኖዶሱ አሳስቧል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ዳር ድንበሯንና አንድነቷን አስጠብቃ የኖረች ሃገር መሆኗን የጠቀሰው ይኸው የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ፣
የህዳሴ ግድብ ከድህነት ለመውጣት አንድ እርምጃ ወደፊት መሆኑን ጠቅሶ የዚህን ግድብ ፍጻሜ በማፋጠን ከጨለማ ለመውጣት መላው ኢትዮጵያውያን እንዲረባረቡ እንዲሁም ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ጨዋነት የሚመሰከርበት ምርጫ እንዲሆንም ጥሪውን አቅርቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣ ከሰኔ 14 ቀን ጀምሮ እስከ ሃምሌ 4 ቀን 2013 ድረስ በመላው ሃገሪቱና በውጭ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ውሳኔ በማሳለፍም አጠናቋል።

LEAVE A REPLY