ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎችን የቫይረሱ ዝርያ በተገኘባቸው ሀገሮች ስም መጥራት፣ የሀገራትን ገፅታ እያበላሸ ነው” በማለት የአለም ጤና ድርጅት “ዝርያዎቹ በግሪክ ፊደላት ይሻላል” ሲል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
እንደ የአለም ጤና ድርጅት አዲስ ሃሳብ ከሆነ፣ የኮቪዲ -19 ዝርያ የሆነውና UK variant ወይንም B.1.1.7 ተብሎ ሚጠራውን “አልፋ” ወደ ደቡብ አፍሪካ የተዛመተውን ደግሞ “ቤታ” ተብለው ቢጠሩ እንደሚሻል ተመልክቷል።
የአለም ጤና ድርጅት ከብራዚል የተገኙ ናቸው የሚባሉትና “P.1” እና “P.2” ተብለው የሚጠሩትን ሁለቱን የቫይረሱ ዝርያዎችን “ጋማ “እና “ዜታ” ብሎ ለመጥራት ያሰበ ሲሆን፣ ሁለቱ ከህንድ የተገኙና “B.1.617.1” እና “B.1.617.2” ተብለው የተለዩ የቫይረሱ ዝርያዎችንም “ካፓ” እና “ዴልታ” ብሎ ለመጥራት ማቀዱን አስታውቋል።