መገናኛ ብዙሃን የሳይበር ደኅንነት እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለጸ!

መገናኛ ብዙሃን የሳይበር ደኅንነት እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለሚድያ ባለቤቶችና ባለሞያዎች የሳይበር ደኅንነትን አስመልክቶ ዛሬ የሙሉ ቀን ስልጠናና ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ መገናኛ ብዙሃን እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ይግዛው ገልጸዋል።

መገናኛ ብዙኀን እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት እውቀት የሌላቸው መሆኑ ጎልቶ በተመላከተበት የዛሬው መድረክ፣ የሚዲያዎች ቴክኖሎጂን የመጠቀምና መረጃን በጥራትና በፍጥነት የማድረስ አቅም እያደገ ቢመጣም፣ ይህን የሚመጥን የሳይበር ደኅንነት ክህሎት አለመኖሩ ግን አሳሳቢ መሆኑን፣ እንዲሁም በመጪው ወራት የሚደረገው ሀገራዊ ምርጫና ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌትን ተከትሎ ሊሰነዘሩ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት ለሚዲያ ባለሞያዎች ግንዛቤ ለመስጠት ማስፈለጉን ዋና ዳይሬክተሩ
አመልክተዋል፡፡

ሚዲያዎች የሚያሰራጩት መረጃ፣ ተዓማኒነቱን ከመጠበቅ ባለፈ ለሳይበር ደኅንነት ትኩረት እና እውቀት መኖር አስገዳጅ መሆኑን ያስረዱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው፣ ሚዲያዎች የሚያሰራጩት መረጃ ተዓማኒነቱን ከመጠበቅ ባለፈ ለሳይበር ደኅንነት ትኩረት እና እውቀት ሊኖራቸው የግድ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

በተያያዘ “የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ለፌዴራል እና የክልል ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎችን ‘ተግባቦት በዲጂታል ዘመን’ እና ‘የቀውስ ግዜ ተግባቦት’ በሚል ርዕስ የልምድ ልውውጥና ሥልጠና እያካሄደ ነው። ይህ ስልጠና በኮሙዩኒኬተሮች መካከል ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ብሄራዊ የግንኙነት ሥነ-ምህዳሩን ለማጠናከር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ አካል ነው” ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY