ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከደቡብ ሱዳን ፕ/ት ሳልቫኪር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ!

ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከደቡብ ሱዳን ፕ/ት ሳልቫኪር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው፣ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክትም ለፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አድርሰዋል፡፡

ሚኒስትሩና ፕሬዚዳንቱ በነበራቸው ውይይት፣ በሁለትዮሽ አገራዊ የጋራ ጉዳዮች፣ በህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ሁኔታ፣ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ እንዲሁም በመጭው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን የገለፀው የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት፣ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራትን የመጉዳት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት ሚኒስትሩ መናገራቸውንም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም፣ ከታችኛው ተፋሰስ አባል አገራት የተውጣጣ የተመራማሪዎች ቡድን፣ ግድቡ የትኛውም ሃገር ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር የሚያስችል ስትራቴጂ መነደፉን፣ ከመጭው ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንደሚካሄድ፣ እንዲሁም መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ለማስወገድ እየሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ማስረዳታቸውንም የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

LEAVE A REPLY