ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በዛሬው ዕለት በተካሄደው ስብሰባ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2014 በጀት ዓመት 561 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በጀት ማጽደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡
በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንደሚያደርገው አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ይህንኑ በገለጹበት ይፋዊ የትዊተርና የፌስቡክ ገጽ መልዕክታቸው “የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2014 በጀት ዓመት የ 561.7 ቢሊዮን ረቂቅ በጀት ዛሬ አጸደቀ፡፡ የ10 ዓመቱን መሪ ዕቅድ መሠረት በማድረግ የማምረት ዐቅማችን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቷል። ይህም ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት ይጥላል” ብለዋል።