መስቀል አደባባይ ነገ ይመረቃል! የሚዘጉ መንገዶች ተለይተዋል

መስቀል አደባባይ ነገ ይመረቃል! የሚዘጉ መንገዶች ተለይተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አወዛጋቢነቱ የቀጠለው መስቀል አደባባይና ከለገሐር እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ነገ በይፋ እንደሚመረቁ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ፕሮጀክቶች ነገ ሰኔ 6/2013 ዓ.ም እንደሚመረቁ አረጋግጦ በዕለቱ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ ኮሚሽኑ መግለጫ ከሆነም የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦

– ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ
– ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ
– ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ
– አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
– ጎላ ሚካኤል
– ጥቁር አንበሳ ሼል
– ሜትሮሎጂ
– ጎማ ቁጠባ
– ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ
– ለገሃር ጉምሩክ መብራት
– ቡናና ሻይ
– ገነት መብራት
– 4ኛ ክፍለ ጦር (ጥላሁን አደባባይ)
– ቂርቆስ መታጠፊያ
– አጎና ሲኒማ
– ኦሎምፒያ
– ኡራኤል አደባባይ
– ባምቢስ መታጠፊያ
– ካዛንቺስ ሼል
– ፍልውሃ ሸራተን አካባቢ መስጊድ
– ኦርማ ጋራዥ
– ንግድ ማተሚ ቤት
– ራስ መኮንን ድልድይ
– አፍንጮ በር ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።

LEAVE A REPLY