ዛሬ በአዲስ አበባ ቦንብ ፈንድቶ አንድ ሰው መጎዳቱን ፖሊስ አስታወቀ!

ዛሬ በአዲስ አበባ ቦንብ ፈንድቶ አንድ ሰው መጎዳቱን ፖሊስ አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዛሬ ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ዮርዳኖስ ሆስፒታል አካባቢ ኤም 7.5 የሚባል ፕላስቲክ ቦንብ ፈንድቶ ቦንቡን ይዞት በነበረው ግለሰብ የግራ እጅ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ለጊዜው ምንነቱ ባልተረጋገጠ ምክንያት ፍንዳታው ዛሬ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ መድረሱን ያመለከተው ፖሊስ፣ ቦምቡን ይዞ የነበረውና አደጋው የደረሰበት ግለሰብ፣ በአካባቢው በጎዳና ላይ ኑሮን በማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ብረታ ብረቶችን በመልቀም የሚተዳደርና ከሶስት ቀን በፊት ስብርባሪ ብረቶችን ሲለቅም ቦንቡን እንዳገኘው መናገሩን ገልጿል፡፡

ግለሰቡ ለህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተላከ መሆኑን፣ በፍንዳታው ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ለማወቅ ምርመራ መጀመሩንና የምርመራ ውጤቱንም ወደፊት እንደሚያሳውቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY