ለፕሬዝዳንቱና ለምክትላቸው ጥብቅ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠ!
ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “የውጭ ምንዛሬ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው እንዲሁም የደቡብ ግሎባል ባንክ የደረሰበትን ኪሳራ በመደበቅና የባንኩ የሂሳብ መግለጫ ትክክለኛ ትርፍ እንዳያሳይ በማድረጋቸው” በሚል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ እና ለምክትላቸው ፍቃዱ ሽጉጤ ጥብቅ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን Fortune Addis በዘገባው አስታውቋል።
ደቡብ ግሎባል በነዚህ ጥፋቶች የተነሣ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ የተቀጣ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው፣ ይህንንም ብሔራዊ ባንክ በኒውዮርክ ሲቲ ባንክ በከፈተው አካውንት ላይ በውጭ ምንዛሬ በቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥ ባንኩ እንዲያስገባ መታዘዙንም አመልክቷል።