ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– 28 አባላት ያሉት የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ስድስተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
የቡድኑ አባላት ምርጫውን ለመታዘብ የሚያስችላቸውን የይለፍ ወረቀት ተቀብለዋል። በዚሁ ወቅት የቡድኑ ኃላፊ አምባሳደር አብዱላሂ አውሌድ አሊ ሜሲ እንዳሉት፤ ተጠባባቂ ኃይሉ በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት ለማረጋገጥ በማለት፣ በተደረገለት ግብዣ መሰረት የምርጫ መታዘቢያ ሥነ ምግባር መርህን በመከተል ለመታዘብ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
የሕግ አስከባሪ አካላት የምርጫው ሂደት የተጠበቀ እንዲሆን ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የጠየቁት ኃላፊው፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና እጩዎች አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱንና የሰዎችን ሰብዓዊ መብት ሊያከብሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።