ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለመዘገብ እስካሁን ድረስ 89 ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ መግባታቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፣ አሀዙ እስከ አሁን ምርጫውን ለመዘገብ ፍቃድ ያገኙ የ29 የውጭ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ብዛት ብቻ መሆኑንና በቀጣይም ጥያቄ አቅርበው ለመዘገብ የሚገቡትን ዝርዝር ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
እስካሁን ባለው መረጃ ጋዘጠኞቻቸውን የወከሉ የውጭ ሚዲያዎች ቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ሮይተርስ፣ ኤ.ኤፍ.ፒ፣ ቪ.ኦ.ኤ፣ ኤ.ፒ፣ ዶቼ ዌሌ፣ ፋይናንሻል ታይምስ፣ ስካይ ብሮድካስቲንግ፣ ከዮዶ ኒውስ፣ አውስታራሊያን ብሮድካስት፣ ዴት ዜይት፣ ዬሌ ብሮድካስት፣ ዣይስ ኒውስ፣ ፍራንክፈርት ሩንዶሽ፣ ዜድ ዲ. ኤፍ ጀርመን ቲቪ፣ ናሽናል ፕብሊክ ሬዲዮ (ኤን ፒ.አር)፣ ቬሪጀስ ሬዲዮ፣ ጃፓን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ስዊድን ደጀንስ፣ ዴር ስተርን፣ ፊኒሽ ብሮድካስቲንግ፣ ትሮው ሚዲያ፣ አሽራቅ ኒውስ ሰርቪስ፣ ኖርዊጂያን ብሮድካስቲንግ፣ ኤጅንሲያ ኤፍ ኤም፣ ሲ.ኤን.ኤን እና ሲ.ቢ.ኤስ መሆናቸውንም ባለስልጣኑ አመልክቷል።