የእናት ፓርቲ ታዛቢ የ8 ሺህ ብር ቅጣት ተወሰነበት!

የእናት ፓርቲ ታዛቢ የ8 ሺህ ብር ቅጣት ተወሰነበት!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዛሬው ዕለት፣ ዘበነ ለማ የተባለ የእናት ፓርቲ የምርጫ ታዛቢ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ መያዙን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አዳነ ጎሹ አስታውቀዋል።

በጮሌ የምርጫ ክልል፣ እናት ፓርቲን ወክሎ ታዛቢ የነበረው ግለሰቡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ በሚሄዱበት መንገድ ላይ እየጠበቀ “ፓርቲውን ምረጡ” በሚል ወረቀት ሲያድል መያዙን የተናገሩት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ፣ ተጠርጣሪው በምርጫ ዕለት የተከለከሉ ተግባራትን በመፈጸሙ 8 ሺህ ብር እንደተቀጣና ግለሰቡ ጥፋቱን አምኖ በመጸጸቱ እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመኾኑ ቅጣቱ እንደቀለለትም ገልጸዋል።

 

LEAVE A REPLY