ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ” ውድ ወንድሜ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ ሁለተኛው ቤትዎ እንኳን ደህና መጡ ብለዋል፡፡
ኬንያ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦረነት በድርድር እንዲፈታ ጠይቃ እንደነበር ይታወሳል። የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጀፈሪ ፌልትማን በቀረቡ ወደ ኬንያ ያመራሉ በተባለበት በአሁኑ ወቅት ነው የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት።
የፕሬዚዳንት ኡሁሩ ጉብኝት ዋነኛ ምክንያት እስካሁን በይፋ አልተገለፀም።