ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የተባበሩት መንግስታት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ጦርነቱ እየተባባሰ ባለበት አካባቢዎች የነብስ አድን የሰብአዊ ዕርዳታ የሚውል 40 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ ድጋፍ መመደቡን አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት የርዳታ ሃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ፥ የገንዘብ ድጋፉ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በጦርነቱ በተጎዱ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል እና ድርቅ ለተከሰተበት ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል አስቀድሞ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተለገሰ መሆኑን ተናግረዋል።
ነገርግን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ለመደገፍ የሚያስፈልገውን የ350 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የሰብአዊ ድጋፍ ተግባራት የ1.3 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት እንዳጋጠማቸው ኃላፊው በመግለጫቸው አሳስበዋል።