ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– እንደ ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ተንታኝና አማካሪ ተቋም ማክ ኪንሴይ ሪፖርት፥ ቻይና በዓለም ከፍተኛ ሃብት በማካበት አሜሪካን በመብለጥ ቀዳሚ ሃገር ሆናለች።
እንደ ብሉምበርግ የቢዝነስ ገለፃ የቻይና ሀብት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በፈረንጆቹ 2000 ሰባት ትሪሊየን ዶላር የነበረው አጠቃላይ ሃብቷ በ17 እጥፍ አድጎ በ2020 ወደ 120 ትሪሊየን ዶላር ማደጉ ተገልጿል፡፡
አሜሪካ ሀብቷን በተመሳሳይ ጊዜ በእጥፍ ያሳደገች ቢሆንም በፈረንጆቹ 2020 ያላት ሀብት 90 ትሪሊየን ዶላር ብቻ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ቻይና ዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት መቀላቀሏ ለኢኮኖሚዋ ማደግና መጨመር እገዛ ማድረጉ ይነገራል።
አሁን ዓለም ላይ ካለው ሃብት ውስጥ 68% የሚሆነው በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ የተከማቸ መሆኑን አር ቲ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።