የኬንያው ፕሬዝዳንት ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃንን መመልከት ያቆሙበትን ምክንያት ገለፁ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃንን መመልከት ያቆሙበትን ምክንያት ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን ለአፍሪካ ያላቸው እይታና አፍሪካን በሚመለከት የሚያሰራጩትን ዘገባ በመረጃ ምንጭነት እንደማይመርጧቸው የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ገለጹ።

አፍሪካ በብዙሃን መገናኛ ተቋማት በአሉታዊ መልክ ብቻ የመገለጽ መጥፎ ዕድል እንደገጠማትም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃንን መመልከት ያቆሙበትን ምክንያት አብራርተዋል። አልጀዚራ፣ ሲኤንኤን፣ ስካይኒውስ፣ ቢቢሲ እና የመሳሰሉት የምእራቡ አለም የሚዲያ ተቋማት በርዋንዳ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኢትዮጵያ አሊያም በሶማሊያ የተከሰቱ ጉዳዮችን ከኬንያ ናይሮቢ ሆነው እንደሚዘግቡ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY