ለዓመታት ኦነግ ሸኔን ሲያገለግል እና ሲመራ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ለዓመታት ኦነግ ሸኔን ሲያገለግል እና ሲመራ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናለዓመታት ሽብርተኛውን የሸኔ ታጣቂ ኃይል ሲያገለግል እና ሲመራ የነበረ እያሱ ዓለሙ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

ግለሰቡ በታጣቂ ኃይሉ ውስጥ አባል ሆኖ በቆየባቸው ዓመታት በውጪ ሀገራት ጭምር የተለያዩ ሥልጠናዎች መውሰዱን እና ለጥፋት ተልዕኮ ተሰማርቶ መቆየቱን ተናግሯል።

በ2007 ዓ.ም ታጣቂ ቡድኑን እንደተቀላቀለ እና በቆየባቸው የጥፋት ዓመታት ከተራ ተዋጊ እስከ ሎጀስቲክስ ኃላፊነት እንደሠራ የገለጸው ወጣት እያሱ የጥፋት ቡድኑ በእንግሊዝ ሀገር የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት እንዲከታተል እና ተመልሶ የሽብርተኛውን አባላት እንዲያሰለጥን እንዳደረገው ገልጿል።

ወጣት እያሱ በሽብርተኛው ሸኔ የጥፋት ተልዕኮ በቆየባቸው ዓመታትም ቡድኑን ከሚደግፉ አካላት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ ተቀብሎ ለታጣቂ ኃይሉ አመራሮች የማድረስ ተግባር እንደፈፀመ ተናግሯል።

LEAVE A REPLY