አዲስ አበባን ጨምሮ በ10 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ሊሰራ ነው

አዲስ አበባን ጨምሮ በ10 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ሊሰራ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜናአዲስ አበባን ጨምሮ በአስራ አንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ማሻሻያ ፕሮጀክት ከ4.7 ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሊተገበር ነው።

በኃይል ማሰራጫ መስመሮች ማርጀት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ እና መዋዠቅ የሚያጋጥማቸውን ከተሞች ጥራት ባለው አስተማማኝ አገልግሎት የሚተካ ፕሮጀክት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚሰራው ፕሮጀክት አዲስ አበባ፣ ነቀምት፣ አምቦ፣ ሱሉልታ፣ ቢሾፍቱ፣ አሰላ፣ ደብረ ብርሃን፣ ዲላ፣ ሆሳዕና፣ አሶሳ እና ጅግጅጋ እንደሚሰራ አገልግሎቱ ገልጿል።

ከ1 ሺህ 610 ኪሎ ሜትር በላይ የመካከለኛ ቮልቴጅ ተሸካሚ መስመሮች የሚዘረጉበት እቅድ ሲሆን ፕሮጀክቱ በ3 ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳስታወቀው ስራውን ለማስጀመር የዲዛይን፣ የግንባታ ግብዓቶች አቅርቦት እና የግንባታ ስራዎችን የሚያከናውኑ ተቋራጮች የሚሳተፉበት የጨረታ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን የግዢ እቅድ ተዘጋጅቶ ለዓለም ባንክ ገቢ ተደርጓል ብሏል።

LEAVE A REPLY