በኮምቦልቻና ላሊበላ ለሰብኣዊ እርዳታ የሚውሉ በረራዎች ተፈቀደ

በኮምቦልቻና ላሊበላ ለሰብኣዊ እርዳታ የሚውሉ በረራዎች ተፈቀደ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኮምቦልቻና ላሊበላ ለሰብኣዊ እርዳታ የሚውሉ በረራዎች እንደተፈቀዱ መግለፃቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈሪ ፊልትማን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ትግራይ ክልልም 369 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ መፈቀዱን የተናገሩ ሲሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን ሁኔታ በተመለከተም ውይይት አድርገዋል።

ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር የሚደረገው ጦርነት ስለሚቆምበት መንገድ የአሜሪካ ሐሳብ ምን እንደሆነ በልዩ መልዕክተኛው በኩል የተነሣ ሲሆን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩም የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል።

አሸባሪው ሕወሓት አሁንም ቢሆን በአፋርና በአማራ ክልሎች ጥቃት እየፈጸመና ከፍተኛ ሰብኣዊና ምጣኔሃብታዊ ውድመት እንዲሁም ሥነ ልቡናዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንና ከሁለቱ ክልሎች ለቅቆ እንዲወጣ ግፊት ሊደረግበት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደመቀ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY