“የወያኔዎች የሰሩትን ወንጀልና ጥፋት ሌላው ላይ ማላከክ ባህላቸው አድርገውታል” አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

“የወያኔዎች የሰሩትን ወንጀልና ጥፋት ሌላው ላይ ማላከክ ባህላቸው አድርገውታል” አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያውያን የተፈጸመባቸውን ግፍና ዘረፋ ትተው በይቅርታ ያለፋቸው ወንጀለኞች በተቃራኒው የኢትዮጵያን መንግሥትና ሕዝብ ለመክሰስና ካሳ ለመጠየቅ ማሰባቸው የሚያሳፍር፣ ወንጀልና ጥፋት መሥራት ባህላቸው ማድረጋቸውን የሚመሰክር መሆኑን ፖለቲከኛ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ገለጹ።

አቶ አንዳርጋቸው እንደገለጹት፤ የወያኔ ሽብር ቡድን እንደ ድርጅት ከተመሰረተ ጀምሮ በታሪኩ የራሱን ወንጀል፣ ጥፋትና ስህተት አምኖ የማያውቅ፣ የሰራውን ወንጀል ሌላው ላይ ማላከክን ባህሉ ያደረገ ነው።
‹‹የዘረፋችሁትን መልሱ፣ ለፈጸማችሁት ወንጀል ተጠየቁ›› መባል የሚገባቸው እነርሱ ሆነው፤ ሕዝቡ የገደሉትን ወልደን፣ የዘረፉትንም ሰርተን እንተካለን ብሎ በይቅርታ ያለፋቸው ወንጀለኞች በተቃራኒው አይን አውጥተው የኢትዮጵያን መንግሥትና ሕዝብ ለመክሰስና ካሳ ለመጠየቅ ማሰብ በራሱ የሚያሳፍር ድርጊት ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያንን ሁሉ ግፍ፣ ዘረፋና የበቀል ወንጀል የፈጸሙበትን ትቶ አገርን በሰላም ለማሻገር ከጦርነት፣ ከበቀል አዙሪት ለመውጣት በማሰብ፤ የገደሉትንም ይቅር እንበላቸው ማለቱንም አስታውሰዋል።

LEAVE A REPLY