ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ 9 ሺሕ 375 ሲም ካርድን ጨምሮ የተለያየ ቁሳቁስ መያዙን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
በከተማዋ አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ሕወሓት የሽብር ድርጊት እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከሲም ካርዶቹ በተጨማሪ 1 ሽጉጥ፣ 5 ላፕቶፕ፣ ሀሰተኛ መታወቂያ እና የሸኔ አርማዎች ከነ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ የፖሊስ መምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ፉፋ መገርሳ ገልጸዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ሕወሓት የሽብር ድርጊት እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ተሳትፎ እንዳደረጉ ኮማንደር ፉፋ አመላክተዋል።