የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ገለፁ

የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በወቅቱም በአገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚመለከት ምክክር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ሄርዞግ እስራኤል እንደ ወዳጅ አገር ለኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅትም ለኢትዮጵያ የአጋርነት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

LEAVE A REPLY