ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ምግብ ምርት እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ።
የአለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ ተቋም ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በላከው መረጃ መሰረት፣ የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ምግብ ምርት ሊስቴሪአ ሞኖሳይቶጅን በተባለ ጎጂና ገዳይ ተህዋስያን መበከሉ ተረጋግጧል።
ስለሆነም፣ ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን እንዲሁም የተመረተበት ቀን ቤስት ከጥር 12/2023 በፊት የሆነ የምግብ ምርት እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳስቧል